አንጋፋው የብስክሌት ተወዳዳሪ አትሌት ገረመው ደንቦባ እና አትሌት ፅጋቡ ገ/ማርያም በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ጽ/ቤት ውስጥ በጋራ መከሩ፡፡

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

በሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ሀገራችንን በብስክሌት ወክሎ የሚወዳደረው አትሌት ፅጋቡ ገ/ማርያም ለውድድሩ ጠንካራ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሠኔ 07 ቀን 2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ጽ/ቤት በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገለጸ፡፡

ሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በ1948 ዓ.ም በተሳተፈችበት የሚልቦርን ኦሊምፒክ ሀገራቸውን በብስክሌት የወከሉት አንጋፋው ኦሊምፒያን ገረመው ደንቦባ በኩላቸው

“ዛሬ ዳግማዊ ልደቴ ነው… እዚህ ተገኝቼ ያለኝን ልምድ ለአትሌት ፅጋቡ ለማካፈል በመታደሌ ልዩ ድስታ ይሠማኛል፡፡”

 

“የአትሌት ፅጋቡ ውጤማነት ኢትዮጵያ በብስክሌት ስፖርት ተተኪዎች እንዳሏት ተመልክቻለሁ፡፡” ብለዋል፡፡

አትሌት ፅጋቡ በበኩሉ “በታላቁ የስፖርት መድረክ፣ ኦሊምፒክ ላይ ተሳትፌ የሀገሬን ስም ለማስጠራት ህልም ነበረኝ“

“ከታላቁ ኦሊምፒያን ገረመው ደንቦባ ጋር ተገኛኝቼ የርሳቸውን ምክር እና የህይወት ተሞክሮ መቅስም መቻሌ  በሪዮ ኦሊምፒክ ውድድር ትልቅ ስንቅ ይሆነኛል“ ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን እና ለ2016 የሪዮ ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ የብስክሌት ቡድን እያደረገ ያለውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡ 

በስተመጨረሻም አትሌት ገረመው ደንቦባ ለአትሌት ፅጋቡ ገ/ማርያም የአደራ መልዕክታቸውን ካስተላላፉ በኋላ በአርማ መረካከብ ሥነ-ስርዓት ተጠናቋል፡፡ 

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result