ኮሜቴው ኦሊምፒዝም በሀገራችን እንዲሰርጽ እና እንዲስፋፋ ለሚዲያ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሠጠ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሀገራችን ኦሊምፒዝም እና የኦሊምፒክ እንቅስቃሴ በሚዲያ ተቋማት ተገቢውን ሽፋን እንዲያገኝ እና እንዲስፋፋ “የብዙሃን መገናኛ ሚና ለኦሊምፒዝም መስፋፋት” በሚል መሪ ቃል ሠኔ 04 ቀን 2008 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ለብዙሃን መገናኛ ኃላፊዎችና ጋዜጠኞች ሠጠ፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴን በተመለከተ አጠር ያለ ገለጻ በኮሚቴው ኤግዚኩዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ታምራት በቀለ ከተሠጠ በኋላ “ኦሊምፒዝም ለማህበራዊ መስተጋብር ያለው አስተዋጽኦ” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቭርስቲ በስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ባልደረባ በሆኑት በዶ/ር ቤኔት ጉዲን እና “ኦሊምፒክ እና የሚዲያ ሚና” በሚል ርዕሠ ጉዳይ ላይ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቭርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙዩኒኬሽን ት/ቤት መምህር በሆኑት በአቶ ተሻገር ሽፈራው አማካኝነት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም “ያለ ብዙሃን መገናኛ ድጋፍ እና አጋርነት የኦሊምፒክ እንቅስቃሴ በመላ ሀገራችን እንዲስፋፋ መፍጨርጨር በአንድ እጅ እንደማጭጨብ ነው”

“ይህ ፕሮግራም ኮሚቴው ከሚዲያ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠናክርለታል” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያዘጋጀውን የኦሊምፒክ መዝሙር በዚሁ መድረክ ላይ አስተዋውቋል፡፡ የኦሊምፒክ መዝሙሩ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የድምጽ መለያ “Brand” እንደሆነም ተወስቷል፡፡  

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result