የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኦሊምፕአፍሪካ የፎትቦል ኔት ውድድር ተጠናቀቀ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የቢሾፍቱ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በጋራ ለሁለት ሣምንታት ያዘጋጁት በስምንት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል ሲካሄድ የነበረው የኦሊምፒክ አፍሪካ የፉት ቦል ቤት ውድደር ሰኔ 05 ቀን 2008 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡

ውድደሩ የኦሊምፕአፍሪካ ፉፉ ቦል ኔት መሰረታዊ መርሆ የሆኑትን ማለትም ታማኝነትን፣ መተባበርን፣ መከባበርን፣ ኃላፊነት፣ ስፖርታዊ ጨዋነት እና መቻቻልን ማዕክል አድርጎ የተከናወነ መሆኑን ታውቋል፡፡

በውድደሩ የማጠናቀቂያ ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ኤግዚኩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ታምራት በቀለ “የፎት ቦል ኔት ውድድር የማሸነፍ የመሸነፍ ጉዳይ አይደለም፡፡” “አላማው በወጣቱ መካከል መከባበርን፣ መተሳሳብን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ለማጎልበት ያለመ ነው፡” ብለዋል፡፡

በሱዳን ሀገር ለሁለት ጊዜ ሀገራችንን ወክለው የተወዳደሩ የከተማው ታዳጊ ወጣቶች በምስራቅ አፍሪካ ከአቻ ሀገሮች ጋር ተወዳድረው ያስመዘገቡት ውጤት አበረታች እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ት/ቤቶች እንደየደረጃቸው የማበረታቻ ሽልማት ከኮሜቴው ተበርክቷላቸዋል፡፡

በስተመጨረሻም የኮሚቴ ኤግዚኩቲቭ ዳይሬክተር የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባስገነባው የኦሊምፕአፍሪካ የስፖርት ማዕከል በተለይ ወጣቶች የእርፍት ጊዜያቸውን ከአልባሌ ቦታ ታቅበው በማዕከሉ በመገልገል አእምሯቸውን እና አካላቸውን በስፖርት እንቅስቃሴ እንዲያዳብሩ አደራ ብለዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያላሰለሰ ድጋፍ እንደማይለያቸው ቃል ተገብቷል፡፡

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result