የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን በኦሊምፕ አፍሪካ ጨዋታ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

በሱዳን-ካርቱም ከግንቦት 17 እሰከ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ የ2008 ኦሊምፕአፍሪካ የፉት ቦል ኔት ውድድር የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን የሦስተኝነት ደረጃን በመያዝ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኦሊምፒዝም ስርፀትና ትግበራ ነዑስ የሥራ ሂደት ባለቤት እና የኦሊምፕ አፍሪካ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ታደለ ሰዴቻ 

“ቡድናችን የሚጠበቅበትን ዝግጅት አድርጎ አበረታች ውጤት አሰመዝግቧል፡፡” አቶ ታደለ ለኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን አባላት “የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እናተን ያፈራውን የቢሾፍቱ ከተማ የኦሊምፕአፍሪካ ማዕከልን ግንባታ ለማጠናቀቅ ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል”

“የቢሾፍቱ ከተማ ማህበረሰብ የህዝብ ሀብት የሆነውን ኦሊምፕአፍሪካ ማዕከልን እንዲከባከብ አደራ እላለሁ፡፡” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የፉት ቦልኔት ቡድን የቡድን መሪውን እና አሠልጣኙን ጨምሮ አስር የቡድን አባላት ያሉበት ጥንቅር ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ ፉትቦል ኔት ቡድን ያገኘውን የሠርተፍኬት ሽልማት ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስረክቧል፡፡ 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result