የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የብራዚል አምባሳደርን በጽ/ቤቱ ተቀብሎ አነጋገረ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብራዚል አምባሳደር ኦክታቮ ኮርቴስ ከሚልቦርን ኦሊምፒክ ጀምሮ ያለውን የኢትዮጵያ እና የኢምፒክ ትሰስርን፣ ስለ ኮሚቴው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የ2016 የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ አትሌቶች የሪዮ ዝግጅት እና ሀገራችን በሪዮ ልታስመዘግብ ስላቀደችው የሜዳሊያ ብዛት ግንቦት 11 ቀን 2008 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ተቀብሎ ባነጋገራቸው ወቅት ገለጻ አድርጓላቸዋል፡፡ 

በመቀጠልም አምባሳደሩ ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሠጥተዋል፡፡

ከውሃ ብክለት ጋር (ከውሃ ስፖርቶች ጋር ተያይዞ) ለቀረበላቸው ጥያቄ አምባሳደሩ ሲመልሱ “የውሃ ብክለቱም መታከሙን እና የማጽዳት ስራውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፣

ከዚካ ባይረስም ጋር ተያይዞም “ዚካ ቫይረስ የብራዚል ቫይረስ አይደለም፡፡ ብዙ ሀገሮች የዚህ ቫይረስ ተጠቂ ናቸው፡፡ ዋናው ጉዳይ የቫይረሱ አምጭ የሆነችውን የወባ ትንኝ ለማጥፋት እየተረባረብን ነው” 

“በሪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ላይ ምንም ስጋት አይግባችሁ፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቶችን እና መላውን የኦሊምፒክ ተሳታፊ በአግባቡ ተቀብለን እናስተናግዳለን፡፡…የሀገሪቱን ፀጥታ ለማረጋገጥም ከ”ኢተርፖል” ጋር በጋራ እየሠራን እንገኛለን፡፡”

 “የመንግሰት ለውጥ ከሪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ ምንም የማይገኛኙ ነገር ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ለአምባሳደሩ ከኮሚቴው ስጦታ ተበርክቷላቸው የአምባሳደሩ የሥራ ጉብኝት ተጠናቋል፡፡   

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result