የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ ጥቅል ትሩፋቶች

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶች በብዛትም በጥራትም መገንባት የተጀመሩት የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ፕሮግራም ከተጀመረ በኋላ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡

በ5ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የተገኙ ዋና ዋና ትሩፋቶች፣

 

1. በሐዋሳ ከተማ ለ5ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታ በሚል የተገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶች (ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሁለገብ ስታዲየሞችና የውኃ ዋና ገንዳዎችን ጨምሮ የሌሎች ስፖርቶች ማዘውተሪያዎች)፣

2. ከምዝገባ ጀምሮ ያለው ሂደት በቴክኖሎጂ ታግዞ መፈጸሙ (ሁሉም ክልሎችና ሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች የስፖርት ልዑካን ቡድኖቻቸውን አባላት በመረጃ መረብ አስቀድሞ ማስመዝገብ መቻላቸው ከተለመደው አድካሚ የማንዋል ስራ ገላግሏል፡፡ 

3. የኦሊምፒክን ደረጃ የጠበቀ የምሽት የመክፈቻና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት፣

4. የኦሊምፒክ ጣዕምና ለዛ ያላቸው ስፖርት፣ ስፖርት የሚሸቱ አቀራረቦች መስተዋላቸው፣

5. ከመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ጀምሮ እስከ መዝጊያው የነበረው አጠቃላይ ሒደት የኦሊምፒክ መርህን የተከተለ መሆኑ፣

6. ሀገራችውን በተለያዩ መድረኳች ሊያስጠሩየሚችሉ ተተኪ ወጣት ስፖርተኞችን የፈራበት፣

7. ጥቃቅን እንከኖች ካልሆኑ በስተቀር ምንም ዓይነት ችግር ሳይፈጠር ስፖርታዊ ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ጨዋታው በሰላም መጠናቀቁ

8. ተሳትፎና የስፖርት ዓይነቶች በቁጥር እና በጥራት መጨመራቸው

ከመጋቢት 4 እሰከ 18 ቀን 2008 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ለሁለት ሳምንታት ሲካሄድ በቆየው 5ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታ አማራ ክልል በኦሎምፒክ ስፖርቶች አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ አማራ ክልል በኦሎምፒክ ስፖርቶች 58 ወርቅ፣ 45 ብርና 67 ነሐሰ ማዳሊያ በመሰብሰብ አንደኛ፣ ኦሮሚያ ክልል በ53 ወርቅ፣ 65 ብርና በ52 ነሐስ ሁለተኛ እንዲሁም አስተናጋጁ ክልል ደቡብ በ43 ወርቅ፣ 38 ብርና 47 ነሐስ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

ቀጣዩንና ስድስተኛውን የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ የመስተንግዶውን ድርሻ ደግሞ የትግራይ መቐለ ከተማ ተረክባለች፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result