በሃዋሳ እየተበሃዋሳ እየተካሄደ ባለው 5ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ኦሮሚያ በቀዳሚነት እየመራ ነው

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

መጋቢት 12 ቀን 2008 ዓ.ም (ኦሊምፒክ) በሀዋሳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው 5ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ኦሮሚያ በቀዳሚነት እየመራ ነው።

ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሜዳሊያ የደረጃ ሠንጠረዥ በገቡበት ዘጠነኛ ቀኑን ባስቆጠረው ጨዋታዎች በኦሊምፒክ ስፖርቶች ኦሮሚያ 42 ወርቅ፣ 45 ብርና 35 ነሐስ በድምሩ 122 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በአንደኝነት ይመራል።
አማራ በ40 ወርቅ፣ 29 ብርና 45 ነሐስ በድምሩ 114 ሜዳሊያዎች በመያዝ ሁለተኛ ነው።
ደቡብ በ25 ወርቅ፣ 27ብርና 30 ነሐስ ሶስተኛ፣ ትግራይ በአስራ ሁለት ወርቅ፣ ሰባት ብርና  አስራ አምስት የነሐስ ሜዳሊያዎች አራተኛ ሆኗል።


አዲስ አበባ በሰባት ወርቅ፣ በስምንት ብርና አስራ ሶስት ነሐስ ሜዳሊያዎች አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቤንሻንጉል ጉምዝ አምስት ወርቅ፣ አምስት ብርና አራት ነሐስ ሜዳሊያዎች ስድስተኛ፣
ድሬዳዋ አስተዳደር በአምስት ብርና ስድስት ነሐስ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሐረሪ ሶስት ብርና አምስት ነሐስ ሜዳሊያዎች በማስመዝገብ ቀጣዩን ደረጃ ይዟል።
ጋምቤላ በአንድ ብርና አንድ ነሐስ ሜዳሊያዎች ዘጠናኛ፣
አፋር ሶስት ነሐስ ሜዳሊያዎችን እና የኢትዮጵያ ሶማሌ አንድ ነሐስ በመያዝ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ገብተዋል።


ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሜዳሊያ የደረጃ ሠንጠረዥ የገቡበት በፓራሊምፒክ ውድድሮች እና የመስማት የተሳናቸው ስፖርት ውድድሮች ውጤት የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ፡፡
5ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በመጪው እሁድ መጋቢት 18 ቀን 2008 ዓ.ም በደማቅ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ይጠናቀቃል።

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result