15ኛው የቤጂንግ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮ በስኬት ተጠናቀቀ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከኦገስት 22 -30/2015 በተካሄደው 15ኛው የቤጂንግ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዓለም የደረጃ ሰንጠረዥ አምስተኛ ደረጃን ይዛ በስኬት አጠናቃለች፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በ800፣ በ1 ሺህ 500፣ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ በ5 ሺህ ሜትር፣ በ10 ሺህ ሜትርና በማራቶን በሁለቱም ጾታዎች 33 አትሌቶች አሳትፋለች። በ1,500 ሜትር ገንዘቤ ዲባባ፣ በማራቶን ማሬ ዲባባና በ5,000 ሜትር አልማዝ አያና አማካይነት ሦስት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች፡፡ በሻምፒዮናው መክፈቻ በተከናወነው የወንዶች ማራቶን የማነ ፀጋዬ፣ በሴቶች 5,000 ሜትር ሰምበሬ ተፈሪና በ10,000 ሜትር ገለቴ ቡርቃ የብር፣ እንዲሁም በ5,000 ሜትር ገንዘቤ ዲባባና በወንዶች ዮሚፍ ቀጀልቻ የነሐስ ሜዳሊያዎች በማግኘት በድምሩ ስምንት ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች፡፡ በውጤታማነት ለተመለሰው የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሻምፒዮናው ሜዳሊያዎች ላመጡ አትሌቶች ከ3ሺህ እስከ 37ሺህ ብር የሚደርስ ሽልማት አበርክቷላቸዋል። እውቅናና ሽልማቱ አትሌቶቹን ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና አትሌት አልማዝ አያና በዚሁ በ15ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5,000 ሜትር ባስመዘገበችው ድንቅ የአጨራረስ ብቃት፣ አዲዳስ ኩባንያ ያዘጋጀውን የወርቅ ጫማ ሽልማት አሸናፊ መሆኗ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result