• 12 August 2017

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት

  • 02 August 2017

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባላት ጋር በስፖርት ልማት ዙሪያ መከረ
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የተመራው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ሐምሌ 24 ቀን 2009 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ እና ከካቢኔ አባላት ጋር በከተማው የስፖርት መሠረተ ልማት ግንባታና የከተማውን ስፖርት ለማሳደግ በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች መክረዋል፡፡
በውይይቱ መጀመሪያ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ለቦርዱ የተደረገውን ደማቅ አቀባበል አመስገነው
“የከተማ መስተዳድሩ የከተማውን ማህበረሰብ በተለይም ወጣቱን በስፖርት ተጠቃሚ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት እስከ ምን ድረስ ነው?::”
“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአዲስ አበባ ወጣቶች የስፖርት ልማት እንደ ወላጅ በመሆን አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው ወይ?::”
“የከተማ መስተዳድሩ በተለይ ከሶስት አመት በኋላ ሀገራችን ለምትሳተፍበት የቶክዮ 2020 የኦሊምፒክ ጨዋታ የዕቅዱ አካል አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ነው ወይ?::” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ካቤኔ ጋር በስፖርት ልማት ዙሪያ መከረ
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የተመራው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ሐምሌ 6 ቀን 2009 ዓ.ም በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሠ መዲና በሆነችው ሠመራ በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረገ፡፡
የስራ አስፈጻሚ ቦርዱ ከክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ከአቶ አወል አርባ እና ከክልሉ የካቤኔ አባላት ጋር በመገናኘት በክልሉ አጠቃላይ የስፖርት ልማት ስራ እንቅስቃሴ ላይ መክሯል፡፡  
በውይይቱ መጀመሪያ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ለቦርዱ የተደረገውን ደማቅ አቀባበል አመስገነው
“የክልሉ መንግስት የክልሉን ማህበረሰብ በተለይም ወጣቱን በስፖርት ተጠቃሚ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት እስከምን ድረስ ነው?::”
“የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለአፋር ወጣቶች የስፖርት ልማት እንደ ወላጅ በመሆን አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው ወይ?::”
“አፋር ላይ እንደሌሎች ክልሎች የስፖርት አደረጃጀቶች ከታችኛው መወቃር (ቀበሌ) እንከ ላይኛው እርከን ድረስ በአግባቡ ተደራጅቷል ወይ?::”  የሚሉ ጥያቄዎችን ካነሱ በኋላ ፕሬዚዳንቱ በመቀጠል


የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን በ2009 ኦሊምፕአፍሪካ ፉት ቦል ኔት ውድድር ሻምፒዩና ሆነ
የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን በአዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ደማቅ አቀባበል ተደረገለት


በሱዳን አዘጋጅነት ከሐምሌ 1-2 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደው የ2009 የኦሊምፕአፍሪካ የፉት ቦል ኔት ውድድር የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነ፡፡

ቡድኑ አሸናፊ የሆነው ሱዳንን ከወከሉ ሶስት የኦሊምፕአፍሪካ ማዕከል ቡድኖች እና ከሶማሌ ቡድን ጋር ተወዳድሮ ነው፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result