Super User

Super User

የቮሊቦል የሁለተኛ ደረጃ የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

ከሀገሪቱ ዘጠኝ ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 30 የቮሊቦል አሠልጣኞች ለአምስት ቀናት የተሰጣቸውን የቮሊቦል ሁለተኛ ደረጃ የአሠልጣኞች ስልጠና ተከታትለው አጠናቀቁ፡፡

ሥልጠናው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከኢንተርናሽናል ቮሊቦል ፌደሬሽን እና ከኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ጋር በጋራ ተዘጋጅቶ የተሰጠ ነው፡፡

 

 

በሥልጠናው የመዝጊያሥነ-ስርዓት ላይ በአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ የተፈረመ ሠርተፍኬት ለሠልጣኞቹ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ በአቶ ታምራት በቀለ ተሰጥቷቸዋል፡፡

 


አዲሱ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በስፖርት ልማት ላይ መከረ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የመጀመሪያውን የስራ ጉብኝት የኮሚቴውን የአመራርነት ኃለፊነት ከተረከበ በኋላ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሚያዚያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም አካሄደ፡፡

የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ሚያዚያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም መቀሌ ሲገባ በክልሉ አመራሮች በአሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ “የስራ ጉብኝቱ አላማ 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ጨዋታዎች የሚተርፈው ትሩፋቶች ፋይዳቸው ከፍተኛ መሆን እንዲችሉ ከወዲሁ የቤት ስራችንን በሚገባ ለመስራት ነው፡፡”

 

 

 

 

መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በተካሄደዉ 42ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተመረጠው አዲሱ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ  ስራ አስፈጻሚ ቦርድ መጋቢት 29 ቀን 2009 ዓ.ም በኮሚቴው ጽ/ቤት በመገኘት ከጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ ስራውን በይፋ ጀመረ፡፡

በቶኪዮ 2020 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ 68 የሚሆኑ አዳዲስ የስፖርት “ኤቭንቶች” እና “ዲስፒሊኖች” እንዲካተቱና እንዲለወጡ ጥያቄዎች ቀረቡ
የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንትና የኦሊምፒክ ጨዋታዎች አስተባባሪ ኮሚሽን ሰብሳቢ የሆኑት ጆን ኮኤትስ በመጪዉ ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ከቀደምቶቹ የኦሊምፒክ ስፖርቶች ውስጥ  የሚቀየሩና እንደ አዲስ የሚካተቱ 68 የስፖርት ኩነቶች እና ዲስፒሊኖች እንዲካትቱ ከተለያዩ የአለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ጥያቄ መቅረቡን  በኦሺኒያ ብሄራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይፋ አድርገዋል፡፡

 

10ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት በ42ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ተመረጡ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም.  ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በአስራ ሁለት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ መክሮ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ከአጀንዳዎቹ መካከል የ2016 የእቅድ አፈፃፀም፣ የፋይናንስ፣ የኦዲት ሪፖርቶች  ለጉባኤው አባላት ቀርበው  ምክክር ተደርጎባቸው በሙሉ ድምጽ ጸድቀዋል፡፡
የኮሚቴው የአራት አመት የስትራቴጂክ እቅድም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
ተቋሙን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ ተካሂዶ ተመራጭ አባላቱ ተለይተዋል፡፡

ለሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የነበረው የፉት ቦል ኔት ትምህርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ


በአስራ ሁለት የቢሾፍቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች መካካል ሲካሄድ የነበረው የፉት ቦል ኔት ትምህርታዊ ውድድር በስኬት መጋቢት 17 ቀን 2009 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡
የቤዛ ትምህርት ቤት የስፖርት መምህር አቶ ብስራት ደስታ “ፕሮግራሙ የሰነቀውን ዓላማ በተለይ ስፖርታዊ ጨዋነትን፣ የቡድን ሥራ እና የስር በርስ መከባባር መንፈስን አስፍኖ በስኬት ተጠናቋል፡፡”
“ከእድሜ ተገቢነት ጋር ተያይዞ ተነስተው የነበሩት ውስን አለመግባባቶች በውይይት መፈታታቸው ደስ ፈጥሯልኛል፡፡” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ 42ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መጋቢት ወር ላይ ያካሄዳል

ኮሚቴውን ለቀጣይ 4 የስትራቴጂክ ዘመን ዓመታት የሚመሩት የሥራ አሰፈጻሚ ቦርድ አባላት ይመረጣሉ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ 42ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሪፍት ቫሊ ሆቴል እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኮሙኒኬሽን ክፍል አስታወቀ፡፡

በ42ኛው የኮሚቴው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤው አባላት በስምንት (8) ጉዳዮች ላይ መክረው ውሳኔ ያሳልፋሉ፡፡

41ኛው (የባለፈው ዓመት) መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ፣2016 የዕቅድ አፈጻጸም፣ የፋይናንስ፣ የኦዲት ሪፖርቶችን፣ የ2017-2020 ረቂቅ ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የ2017 ዓመታዊ ዕቅድ፣ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ ማስፈጸሚያ ረቂቅ መመሪያን መርምሮ ማፅደቅ፣ በመጨረሻም ተቋሙን ለቀጣይ 4 ዓመታት የሚመሩትን የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ ይካሄዳል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ለ4 ዓመታት ለመምራት ለመወዳደር የሚፈልጉ የስፖርት ማህበራት ዕጩ ተወዳዳሪያቸውን ጠቅላላ ጉባኤው ከመካሄዱ አስራ አምስት ቀናት በፊት መርጠው እንዲያቀርቡ በመመሪያው በተደነገገው መሰረት ፍላጎት ያላቸው ማህበራት እስከ እጩ ማቅረቢያው የመጨረሻ ቀን መጋቢት 8 ቀን 2009 ዓ.ም 11፡30 ድረስ አስራ አምስት (15) ተወዳዳሪዎች ቀርበዋል፡፡

 

 

 

”የኦሊምፒክ እና የፓራሊምፒክ ጨዋታዎችን ለአዘጋጅ/ለአስተናጋጅ ከተማ ከአስራ አንድ አመት በፊት እንዲያዘጋጅ መፍቀድ የኦሊምፒክ ቻርተርን ይጥሳል ተባለ”
“የሚጣስ የኦሊምፒክ ቻርተር የለም…በስፖርቱ ውስጥ ያለውን ተለዋዋጭ ሁኔታ በማጤን የማዘጋጀት እድሉን ከተለመደው ሰባት ዓመት ቀድሞ መስጠት ወቀቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡” የአለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማህ ባህ

 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የፉት ቦል ኔት ትምህርታዊ ውድድር የቢሾፍቱ ታዳጊ ወጣቶችን የቡድን ስራ ያሳድጋል ተባለ
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዘጋጅነት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የኮሚቴው ኦሊምፕአፍሪካ የስፖርት ማዕከል የፉት ቦልኔት ትምህርታዊ ውድድር በአስራ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ታዳጊ ተማሪዎች መካከል መጋቢት 9 ቀን 2009ዓ.ም ተጀመረ፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result